የቀጠለዉ የሙስሊሞች ተቃዉሞና ርምጃ
ኮፈሌ አርሲ ዉስጥ በሳምንቱ ማብቂያ የፀጥታ አስከባሪዎች በተሰባሰቡ የከተማይቱ ኗሪዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች መግደል እና ማቁሰላቸዉን የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሚቆጣጠረዉ ቴሌቪዥን ጣቢያ በበኩሉ አሸባሪዎች ካላቸዉ ወገኖች ፀጥታ
አስከባሪዎች ሶስት መግደላቸዉንና ሰባት የፖሊስ አባላትም መቁሰላቸዉን ትናንት ዘግቧል። እንደሌሎች መገናኛ ብዙሃን
ዘገባ የሟቾች ቁጥር 25 ይደርሳል፤ ከአንድ ሺህ በላይም ታስረዋል። ሁኔታዉን እንዲያጣራ የጠየቅነዉ ዘጋቢያችንን
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔርን ሸዋዬ ለገሠ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስልክ አነጋግራዋለች፤
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment