Monday, August 5, 2013

አጭር ወሬ፤ በኮፈሌ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ነው…

Posted by Mesfin Tadese  

05image0D2jpg-2557768_p9አጭር ወሬ፤ በኮፈሌ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ነው…
አርብ እለት ለገደላ ሲያሟሙቁ የነበሩት የመንግት ወታደሮች ብሉሃን ኢትጵያውያን ሙስሊሞች በወሰዱት ብልሃት የተሞላበት እርምጃ የመግደል አምሮታቸው ኩም ብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን በአርሲ ኮፈሌ የተሰማሩት ተኳሾች አንዴ ከመጣን አንመለስም በሚል በከፈቱት ተኩስ በርካታ ንጹሃንን ለሞት፣ በርካታ ምስኪኖችን ለጉዳት፣ በርካታ ዜጎችንም ለእስር ዳርገዋል፡፡
የሟቾች ቁጥር አስመልክቶ እነ ኢቲቪ ሶስት ሰው ሞተ ሲሉ ሲኤን ኤን አይ ሪፖርት ላይ የወጣው ወሬ ደግሞ 25 ሰዎች መገደላቸውን ናገራል፡፡ ከእኛ እንደ አንዱ የሆኑት እነ ኢሳት እና እነ ኢካዴፍ ድረ ገፆች የሟቾቹ ቁትር 11 ደርሷል ሲሉ አውርተዋል፡፡
የሆነው ሆኖ በኮፈሌ አሁንም ውጥረት እንዳለ ከወደኮፈሌ አንድ ወዳጄ ነግሮኛል፡፡
ዘርዘር ያለ ነገር እስክናወራ ድረስ የመንግስት ወታደሮች መተኮስ ብቻ ሳይሆን ማመዛዘንም እንዲለማመዱ አንመክራለን፡፡
ቀን ያልፋል… የምንሰራው ስራ ግን ይቆያል፡፡ ነገ የማንፀፀትበትን እንስራ ብለን ለሚሰማ እንናገራለን!
source: http://www.abetokichaw.com

No comments:

Post a Comment