Saturday, July 27, 2013

ወዴት እያመራን ይሆን ???

በመስፍን ታደሰ
July 27, 2013
ወዴት እያመራን ይሆን ???
የቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ የሙት ዓመት በአሁኑ ሰዓት በመላው ኢትዮጲያ እየተከበረ ይገኛል። የትምህርት ሚንስትር ሠራተኞችና የከተማ ልማትና የቤቶች ኮንስትራክሽን መስሪያ ቤቶች ሠራተኞች አንድ አዳራሽ ውስጥ ታድመዋል። ከተሰብሳቢዎቹ መካክል የሆነ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የነገረን ተሰብሳቢ እንደተናገረው በስብሰባው የተገኝነው ወደንና ፈቅደን ሳይሆን አስገድደውን ነው በማለት ሁኔታው ያበሳጨው መሆኑን ሲገልጽ በምሬት እንዲህ ሲል ተደምጧል ''በጣም አስገራሚ አገር ሁናለች እኮ ፥ ተገደን ፈርመን ነው እኮ ነው ስብሰባው ላይ የተገኝነው''። ከዚህ በተጨማሪም በስብሰባው የታደሙት ሠራተኞች ስሜታቸው ምን እንደሚመስል ተጠይቀው ሲናገሩም እንዲያው ግዴታ ሆኖብን መገኝት ሲላለብን ነው እንጂ ማንም የሚሰማችው ሰው የለም፥ ሁሉም ደብሮታል። የኢንተርኔት መስመር ያላቸው ሠራተኞች ሞባሎቻቸውን ከፍተው ቻት ማድረግና ፎቶዎችን ካልታገዱ ድረ- ገጾችና ፌስ ቡክ እየተመለከቱ የስብሰባውን ማብቂያ እየተጠባበቁ ነው።


''እኔስ ወዴት እያመራን እንደሆነ ማወቅ እስኪሳነኝ ድረስ ገራ ግብት ቢሎኛል አምላክ ምህረቱ ያውርድልን ለአገራችን'' በማለት አስተያየቱን የሰጠን ከዝያው ከስብሰባው መሃል
ዳሚ ሆኖ ነው። ወገን ለመሆኑ ምን እየሰማን ይሆን? 

አስተያየትዎን ያስቀምጡ።