Sunday, April 21, 2013

                Posted By  Mesfin Tadesse

ኖርዌይ የተደረገው የወያኔ ገቢ ማሰባሰቢያ አዳራሽ ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጠሩት!! video 
Ethiopians in Norway raised Ethiopian flag
በኖርዌይ የሚታተመው አፍተንብላደ( Aftenbladet)ጋዜጣ እንደዘገበው ለአባይ ግድብ በተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ የወያኔ ባንዲራ ተሰቅሎ የነበረ ሲሆን ተቃዋሚው  ባንዲራውን በመሸፈን ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ባንዲራ  ሲሰቅል የሚያሳይ ዘገባ ይዞ በፎቶ ወቷል። ወደ ኖርዌይ ትጉዛ ተዋርዳ የተባረረችው የወያኔ ዲፕሎማት ጀሌ በስዊዲን ወይዘሮ መብራት በየነ ሲደነግጡ ታይተዋል::

ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ጭቅጭቅ ነበር። ተቃዋሚዎች አይገቡም በማለት የተጀመረው መክፈቻ በኋላ ላይ ግን ፖሊስ ከመጣ በኋላ እንዲገቡ ተፈቀደ ። ስብሰባው በጥያቄ ተጀምሮ ነበር። ተቃዋሚዎቹ ጥያቄውም እንዲ በማለት ጀመሩ፥
1 በመጀመሪያ እስከዛሬ እናንተ ከገባችሁ ጅምሮ ለገደላችሁት ሰዎች የህሊና ፀሎት ይደረግ በማለት ነበር የተጠየቀው በመቀጠል
2 እስከዛሬ እናንተ ያደረጋችሁትን የዘር ማጥፋት በአማራ፣ በኦሮሞ እንዲሁም በሕዝባችን ላይ የተደረገው ነገር ሳያንስ ዛሬ ደግሞ በአማራው ላይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ እየፈፀማችሁና እየገደላችሁ እዚህ መጣችሁ ገንዘብ መጠየቅ ለኛ ድፍረት ነው በማለት በስብሰባው አዳራሽ በጩወትና በመፈክር ተናወጠ የወያኔ የስዊዲን አገር ቆንፅላም እንዲሁም ጀሌዎቹም በመፍራት አዳራሹን ለተቃዋሚዎች በማስረከብ ለቀው ወተዋል ! ።
ሌባ ነው ሌባ ወያኔ ሌባ በማለት የተጀመረው በመፈክር በጭወትና በዝማሪ አዳራሹ ተደበላልቋል!
ከገንዘብ በፊት ነፃነት ይቅደም!
ከገንዘብ በፊት ሰብኣዊነት ይቅደም!
ኢትዮጵያ አገራችን የደፈረሽ ይውደም! በማለት ተቃዋማቸውን ሲያሰሙ ነበር።
 የወያኔ/ ህውሃትና ጀሌዎች በአለም ላይ የሚያደርጉት የአባይ ገቢ ማሰባሰብያ በየአለማቱ ተቋውሞ እየደረሰበት ይገኛል።
በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ሳይሳካ እንደውም ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት ያሳዩትን ጀግንነት ቀጥሎ በሌሎች አገርም በአሜሪካ፣ በሳውዲ አረቢያ( ጅዳ) ፣በጀርመን ተቀጣጥሎ በቀጠለበት ሁናቴ በኖርዌይ ከፍተኛ የሆነ ተቋውሞ ደርሶበታል ።
በኖርዌይ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ስብሰባ በመቃወም ወያኔ የተከራየውን ገቢ ማሰባሰብያ አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት የወያኔን ባንዲራ በማውረድ የኢትዮጵያን ትክክለኛውን ባንዲራ በመስቀል በማውለብለብ ወያኔዎችንና ጀሌዎችን በማባረር አዳራሹን ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል ። በአለማቱ ያሉቱ የወያኔ ቅጥረኛ አምባሳደር ተብዬዎች አንገታቸውን ያስደፋና እንደ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተራቸው አንገትን አስደፍቶ፣አስደንግጦ ወደ መጡበት ያስመለሰ ነበር።አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ሙሉ በሙሉ ይበልጣሉ።ታሪክ በውጪ ባሉ ኢትዮጵያዊያን እየተሰራ ይገኛል!
 ኢትዮጵያውያን አንድነታቸው ተጠናክሯል ። የወያኔ የመገነጣጠል አላማ ስትራቴጂ የወደመበት ሆኗል።የሕዝቡም አንድነት የታየበት ነበር።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍም ሚያዚያ 18 2013 መካሄዱ ይታወሳል።
ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ በመሆን በመዘመርና በመፍክር ብሶታቸውን አሰምተዋል።
ተቃዋሚዎቹ በአንድነት በመሆን ያሰሙት ቃል ነበር
(( ገና ይቀጥላል ሁላችንም ነፃ እስከምንወጣ ድረስ ))
ሞት ለአንባገነን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

Saturday, April 20, 2013

የወያኔ ባለስልጣናት የፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊቱን ለተጠንቀቅ የሚዘጋጅበትን ሁኔታ መከሩ::

ባለፈው የአከባቢ ምርጫ ህዝቡ ለወያኔ የሰጠውን የድምጽ ስውር መልእክት የስርኣቱን ተባዎች ያስደነገጣቸው ስለሆነ ዋና መወያያ ርእስ ከመሆኑም በተጨማሪ በካድሬው አከባቢ በስፋት እያነጋገረ ሲሆን አስደንጋጭ ድንገተኛ የራስ ውዝግብ የፈጠረባቸው የወያኔ ባለስልጣናት እና ጀነራሎችን ስለ ተከታዩ ትላንት ለሊቱን ሲወያዩ አድረዋል::

የዚህን ምርጫ ዉጤት ተከትለው ተቃዋሚ ሃይሎች ለፖለቲካ ፍጆታቸው ብሶት ያለበትን ህዝብ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: በሚል ፍራቻ እንዲሁም መንግስታዊ መዋቅሮች ተዛንፈው ለወያኔ አደጋ እንደፈጠሩበት አድርገዋል:: የክልል ባለስልጣናት ስልጣናቸውን ያለኣግባብ በመጠቀም በማናለብኝነት የሚፈጽሙት ድርጊት ለኢሕኣዴግ ውድቀቱን እያፋጠነ ነው::አይን ያወጣ በልቼ ልሙት የሚል የቶሎ ቶሎ ኪራይ ሰብሳቢነት/ሙስና/ መንሰራፋቱ ኑሮ ዉድነት እንዲከሰት ምክንያት ሆኗአል በሚል ዙሪያ እና በሙስሊሙ ጉዳይ ዙሪያም እንዲሁ ተመክሯል:;

የአከባቢ ምርጫ የህዝቡ ብሶት ተንጸባርቆበታል ስለዚህ ተቃዋሚ ሃይሎች ይህ ነገር የልብ ልብ ስለሰጣቸው ህዝቡን ቀስቅሰው የራሳቸውን አብዮት ሊሰሩ ስለሚችሉ የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊቱ በተጠንቀቅ እንዲቆም አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግ ለጄኔራሎቹ እና ለፖሊስ ባለስልጣናት የተነገራቸው ሲሆን ተቃዋሚዎች በሰላማዊ ተቃውሞ ስም የሚያደርጉት ማንኛውንም እንቅስቃሴ ወደ ግርግር ለመለወጥ እና ህዝቡን ዝም ለማሰኘት እንዲሁም ተቃዋሚዎችን ወደ ውህኒ ለማውረድ አስፈላጊው ሁሉ እንዲሰራ ለደህንነት ባለስልጣናትም መመሪያ ተሰቷል::

የክልል ባለስልጣናትን በተመለከተ በትእግት ድንገተኛ እርምጃ በመውሰድ ከስልጣን ማባረር እና ተጠያቂ የሚሆኑበትን ሰበብ ፈልጎ ህዝቡን ለማረጋጋት ወደ እስር ቤት መወርወር...እንዲሁን በምትካቸው ከፌዴራል መንግስት የተደራጀ እንቅስቃሴያቸውን የሚቆጣጠር ኮሚቴ ተዋቅሮ በየክልሉ እንዲመደብ ሲሉ የትግራይ እና የኣማራ ክልልን ይህ የኮሚቴ ምደባ አይመለከተውም በሚል ተስማምተዋል::

ሙስናን በተመለከተ ሁሉም የያዘውን ይዞ ለጊዜው ረገብ እንዲል እና በኢንቨስተሮች በሃገር ዉስጥ ነጋዴዎች ላይ እየተደረገ ያለው ማነቆን ረገብ ለማድረግ ሲወያዩ... በሃገር ውስጥ ያለው የወያኔ የንግድ ተቋማት ገንዘቦች ወድ ተለያዩ የአፍሪካ ባንኮች ውስጥ በዶላር እንዲቀመጡ ሃሳብ ቀርቦም ነበር:;ባሃሳቡ መሰረት ሁኔታዎች ታይተው አስቸኳይ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎ ታልፏል::የሙስሊሙም ጉዳይ ከተለያዩ አካላት ጋር እየተነጋገርን እና እየተደራደርን ስለሆነ የፍርዱ ሁኔታ እንዲዘገይ አድርገናል መፍትሄው እየተጠና ነው ቢባልም ብዙ ትኩረት ተሰቶት እንዳልተወያዩበት የብኣዴን ነባር ታጋይ የሆኑ የውስጥ አዋቂ ምንጫችን
ያደረሱን መረጃ ይገልጣል::

ምንጭ ምንሊክ ሳልሳዊ

የአውሮፖ ህብረት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የህዝቡ ነጻነት እንዲከበር ጠየቁ

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ መሪ ማርቲን ሹልትዝ ፣ የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ሚስተር ጆሴ ማኑኤል የጎበኙት ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ባሮሶ እና የካውንስሉ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ቫን ሩምፒ፣ ኢትዮጵያ በእሰር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ርእዮት አለሙን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሀዝቡ ነጻነት እንዲከበር፣ የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሻሻል፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ እንዲከለስ ለጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጥያቄ አቅርበዋል። ባለስልጣናቱ ጥያቄውን ያቀረቡት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የአውሮፓን ህብረት በጎበኙበት ወቅት ነው።

... ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላም ለማስከበርና ሽብረተኝነትን ለመዋጋት እንዲሁም ድህነትን ለመቅረፍ ለማታደርገው ጥረት እውቅና እንደሚሰጡ የገለጡት ባለስልጣናቱ፣ ይሁን እንጅ ትክክለኛ ልማት የሰው ልጆች ነጻነት ሳይከበር የሚመጣ ባለመሆኑ ፣ መንግስት የዜጎቹን ነጻነት እንዲያከበር ጠይቀዋል።

የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ባሮሶ የሰብአዊ መብቶች ሁሉም የሰው ልጆች ሊያገኙዋቸው የሚገቡ አለማቀፍ መብቶች መሆናቸውን ለአቶ ሀይለማርያም ገልጸውላቸዋል። የካውንስሉ ፐሬዛድንት በበኩላቸው “ የማህበራዊ ልማት ስኬት የሚለካው በጠንካራና ግልጽ በሆነ ማህበረሰብ እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የሰው ልጆች መብቶች ሲከበሩ ነው በማለት ተናግረዋል፡

አቶ ሀይለማርያም በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲሰፍን፣ የዜጎች መብቶች አንዲከበሩና የሲቪክ ማህበረሰቡ ሚና አንዲጎለብት ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ሶስቱም የ አውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ችግሮች ላይ ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚካሄደው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ትኩረት መስጠት መጀመሩን እንደሚያመለክት የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። ከአሁን በፊት የህብረቱ ኮሚሽንና ካውንስሉ በኢትዮጵያ ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ትኩረት ሰጥተው እንደማያውቁ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሚስ አና ጎሜዝ የሚሳተፉበት ፓርላማ በተደጋጋሚ የሚያወጣቸውን መግለጫዎች በተለይ ኮሚሽኑ ውድቅ ሲያደርጋቸው ቆይቷል። ከአቶ ሀይለማርያም ጋር በነበረው ስብሰባ ሶስቱም የህብረቱ የስልጣን አካላት አንድ አይነት አቋም ማራመዳቸው ለሰብዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ስኬት ለኢትዮጵያ መንግስትም ከእንግዲህ የሰብአዊ መብቶችን እየጣሱ ዝም ብሎ ሊታለፍ እንደማይችል ትምህርት የሚሰጥ ነው በማለት አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የህዝቡ ነጻነት እንዲከበር ጠየቁ
ሚያዚያ  ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ መሪ ማርቲን ሹልትዝ ፣ የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ሚስተር ጆሴ ማኑኤል  የጎበኙት ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ባሮሶ እና የካውንስሉ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ቫን ሩምፒ፣ ኢትዮጵያ በእሰር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ርእዮት አለሙን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሀዝቡ ነጻነት እንዲከበር፣ የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሻሻል፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ እንዲከለስ ለጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጥያቄ አቅርበዋል። ባለስልጣናቱ ጥያቄውን ያቀረቡት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የአውሮፓን ህብረት በጎበኙበት ወቅት ነው።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላም ለማስከበርና ሽብረተኝነትን ለመዋጋት እንዲሁም ድህነትን ለመቅረፍ ለማታደርገው ጥረት እውቅና እንደሚሰጡ የገለጡት ባለስልጣናቱ፣ ይሁን እንጅ  ትክክለኛ ልማት የሰው ልጆች ነጻነት ሳይከበር የሚመጣ ባለመሆኑ ፣ መንግስት የዜጎቹን ነጻነት እንዲያከበር ጠይቀዋል።