Sunday, April 28, 2013

ሰበር ዜና!


Oromo-Norwegians Stage Protest Against Neo-Neftegna TPLF in Oslo – 11 Arrested for Civil Disobedience

Gadaa.com
According to a Norwegian paper dagbladet.no and Google Translate service, Oromo-Norwegians protested against TPLF officials who were holding a meeting at the luxurious 4-Star Radisson Blu Scandinavia Hotel in Oslo, Norway, on April 28, 2013. The paper also said 11 were arrested for a short-period for civil disobedience, a form of nonviolent protest.
The Neo-Neftegna TPLF, which has been militarily occupying Oromiyaa since 1991, was forced to cancel its meeting. TPLF is using the overseas meetings to divert the attention from the ongoing land-grabs (farmland thefts), deforestation and gross human rights violations, including lack of press freedom, in Oromiyaa and elsewhere in the colonized South of the Ethiopian empire.
More coverage here:
The Gulele Post
Ayyaantuu.com
Gadaa.com



ሰበር ዜና! ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ዛሬም በኦስሎው፣ ታሪክ ሰሩ!


ወያኔ በልማት ስም ገንዘብ ለመቃረምና ደጋፊ ለመመልመል አቅዶ ከሳምንት በፊት በስታቫንገር አንዲሁም በዛሬው እለት ደግሞ በኦስሎ ስብሰባ ለመጥራት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካላቸው የውርደት ካባቸውን ለብሰው መሄድ እጣፋንታቸው እንዲሆን የግድ ሆኗል፡፡ እንደሚታወቀው ባለፈው ሳምነንት ማለትም እንደ ኢሮፓ አቆጣጠር ሚያዝያ 20፣ 2013 በነበረው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያዊያን ከየተለያዩ ቦታዎች በመሰባሰብ የወያኔ አምባሳደር በስዊድን የሆኑትንና የዲያስፖራ ተወካዩን ከስብሰባ በማባረር ከፍለውበት የነበረውን አዳራሽ ተረክቦ ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን አጀንዳ እና ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን እርዳታ የሚሆን ገቢ እንዲሰበሰብና ይህን አምባገነንና ዘረኛ ቡድን መታገል የሚቻለው በ አንድነት መሆኑን ሁሉም የሚስማሙበትና እጅ ለእጅ ተያይዘን መታገል እንዳለብን አስምረው፣ ከ አንድ ሳምንት በሗላ ለሚደረገው የወያኔ ገቢ ማሰባሰቢያ ይህንኑ ድል መደገም ያለበት መሆኑን በመስማማት ነበር የተለያዩት፡፡
ይህንንም ተከትሎ የስታቫንገሩን የወያኔ ፕሮግራም ለማክሸፍ ከፍተኛው ሚና የተጫዎተውን ግብረ-ሓይል በማጠናከር ሳምንቱን ሁሉ ውጤታማ ሥራ ለማድረግ የሙስሊም ወንድሞቻችንን፤ ኦሮሞና ሶማሌ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር ሌት ከቀን  ሲሰራ ሰነንብቷል፡፡ የጀግኖች ኢትዮጵያዊያንን ከፍተኛ ዝግጅትና ቅስቀሳ ሲከታተሉ የነበሩ የወያኔ ቅጥረኞችና አገላጋዮች ስብሰባ ሊደረግ ታቅዶበት የነበረውን አዳራሽ የስብሰባው ሰዓት ሊደርስ አንድ ሰዓት ተኩል ሲቀረው የመሰብሰቢያው አዳራሽ በፀጥታው፣ በጥራቱና በደህንነቱ በታወቀው ራድሰን ብሉ ሆቴል እንደሚካሄድ አስታውቀው፣ ስብሰባውን ለመሳተፍ ግን ህጋዊ መታወቂያ እንደሚያስፈልግ ተገልፆ የሞባይል አጭር መልዕክት ተላለፈ፡፡ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ስብሰባው ይካሄድበታል ተብሎ ከታሰበበት አዳራሽ አካባቢ ከአስር ሰዓት ጀምሮ ወደዚያ የሚያልፈውን የወያኔ ቅጥረኛ ለመቃኘት ወረውት የነበረ ቢሆንም ዘግይቶ የመጣውን አጭር የሞባይል መልዕክት ማለትም የስብሰባ ቦታ መቀየር በመረዳት፣ ወደዚያው ተመመ፡፡
ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊያን ከመድረሳቸው በፊት በገቡት የወያኔ ተወካዮች በመበሳጨቱ ወደ ሆቴሉ ለመግባት በነበረው ግብግብ፣ ምንም ዓይነት ሰው እንዳይገባ ተከለከለ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያዊያንን ቁጣ ለማስቆም ከ15 መኪና በላይ የፖለስ ሃይል የተጨመረ ቢሆንም የጀግኖች ኢትዮጵያዊአንን ቁጣና እልህ መቋቋም አልቻሉም ነበር፡፡ አካባቢው የግልና ተቃውሞውም ህገወጥ እንደሆነ በማስረዳት  ከአካባቢው ገለል ለማድረግ ቢሞክሩም አልተቻለም፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በሆቴሉ የታደሙት የወያኔ ቅጥረኞት ወጥተው ካልሄዱ አካባቢውን ለቀን አንሄድም፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለንበማለት አብዘተው ጮሁ፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሁለት ሴቶች እህቶቻችንና ዘጠኝ ወንድሞቻችን ለሰዓታት ታስረው የተፈቱ ሲሆን፤ ፖሊስም የተቃውሞውን ሓይለኝነት በማየት የወያኔ ተወካዮችንና የስብሰባው አስተባባሪዎች በጓሮ በር ማለትም በመኪና ማቆሚያ በኩል ከህዝብ ሰውረው ከሆቴሉ ሸኝተዋቸዋል፡፡
ከዚያም ኢትዮጵያዊያን አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ፤ አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ፤ አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ እያሉ በመዝለል ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሚከተሉትን የፎቶ ትዕይንት ይመልከቱ፡፡
DSC_0010DSC_0012DSC_0015DSC_0922DSC_0931DSC_0938Arrestationarrestation 2.

 posted by Mesfin Tadesse
sources: gedda.com , ethioviews.com

No comments:

Post a Comment